Saturday 23 July 2022

NIZENU Center Coming


NIZENU Personal and Professional Development Center is coming with bold strategy and mission




Saturday 29 January 2022

የልደትና ጥምቀት በአላት ግሩም ትዝታዎች

 በ በሁለተኛው ሺ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን አስራ አራተኛው አመት ላይ የተከበሩት የልደት/ገናና ጥምቀት በአላት ልዩ ትዝታ የነበራቸው ናቸው።

ፎቶዎች እንደሚናገሩት ከቤተሰብ ጋር የነበረው መስተጋብር እጅግ ልብ የሚጠግንና ተስፋ የሚሰጠሰ ነበር። በጤና ኖሮ ሁሉንም ነገር ማየት መታደልም መመስገንም ነው።

የእድሜና የጤና ጌቴ ከተቤዠን ብዙውን እናገኛለን። ደስታችንም ይበረክታል።

በፈጣሪ እናት በእመቤታችን ፀሎት ምልጃና በረከት ተከበን አመታት አለፉ፤ ያልፋሉም።

ምስጋና በረከትን ስለምታመጣ ተስፋን ስለምትሰጥ ማመስገን ብልሀት ነው።
























Monday 6 December 2021

Business for Development Interview

የአፍሪቃ ነፃ ገበያ እና ጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ መንግስት የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት አቅም ማጎልበት ይጠበቅበታል፤ 

አቶ ጌታቸው መላኩ 

የፓንአፍረቃ ን/ምክር ቤት አማካሪ


የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በመላው አለም 90 በመቶ የሚሆኑት ቢዝነሶች የሚንቀሳቀሱት በጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ደረጃ ነው። እነዚህ ተቋማት ከግማሽ በመቶ በላይ የስራ እድል የመፍጠር አቅም አላቸው። እ.ኤ.አ በ2018 የአለም ባንክ ባወጣው ሪፖርት በመላው አፍሪቃ 415 ሚሊዮን ህዝብ በከፋ ድህነት ውስጥ ይገኛል ። ይህ ቁጥር በአለማችን ድህነት ውስጥ ከሚገኙት 57 በመቶ ድርሻ ይሸፍናል ። የአለም ባንክ መረጃ መሰረት የዛሬ 15 ዓመት ገደማ እጅግ በከፋ ድህነት ውስጥ ላሉ አፍሪቃዊያን በ10 ነጥብ 9 በመቶ ድህነቱ እንደሚቀንስ ትንበያውን አስቀምጧል ። የአፍሪቃ አሕጉር ነጻ የንግድ ቀጠናው በሙሉ አቅሙ ተግባራዊ ሲሆን ተጨማሪ 30 ሚሊዮን ህዝብን እጅግ ከከፋ ድህነት ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የፓን አፍሪቃ ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ እና ኢንዱስትሪያል ፕሮጄክት አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው መላኩ እንዳሉት ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት የስራ እድል በመፍጠር ድርሻቸው ከፍተኛ ነው። ይሁን እና ከአፍሪቃ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ጋር በተያያዘ ዘላቂ ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የመክራሉ። ለአብነትም በቀጠናው የሚከናወን የኢትዮ -ጅቡቲ ኮሪደርን አንስተዋል ። ኮሪደሩ በቀጠናው የገቢ እና የወጪ የቢዝነስ እንቅስቃሴ ዋና ተጠቃሽ ነው ። የኮሪደሩ ልማት በተለይም ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት የስራ እድል መፍጠር ብቻ ሳይሆን የስራውን ዘላቂነት ያረጋግጣል ። ለማሳያነትም በኮሪደሩ መስመት በየቀኑ በመቶዎች የሚሽከረከሩ መኪኖች በመኖራቸው ለመኪኖቹ የሰርቪስ ስራ የሚሰሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ማደራጀት ተጠቃሚነታቸውን ያሳድጋል ብለዋል። ከአፍሪቃ መደበኛ ባልሆነው ሀገር አቋራጭ ንግድ ላይ ከተሰማሩ አንቀሳቃሶች ውስጥ ሴቶች 70 በመቶውን እንደሚያዙ ይገመታል ። በዚህ ስራ ላይ ተሰማርተው ያሉ ሴቶች ለጥቃት፣ ለመብት ጥሰት፣ ለሸቀጦች መወረስ፣ እናለእስራት የተጋለጡ ናቸው። 

የአፍሪቃ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ታሪፍን በመቀነስ መደበኛ ባልሆነ ዘርፍ ለተሰማሩ ነጋዴዎች የተሻለ ከለላ በሚሰጠው ወደ መደበኛ ዘርፍ እንዲገቡ ሊያደርግ ይችላል። እንደ አቶ ጌታቸው ገለፃ ፣ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት በተለይ ለሴቶች የስራ እድልን በመፍጠር የጎላ ስተዋፅኦ አለው። ጥናቶች እንዳረጋገጡት በሴቶች የሚመሩ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት በወንዶች ከሚመሩቱ በተሻለ መጠን የስራ እድል ፈጥረዋል ። አሁን ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው 6 ነጥብ አንድ በመቶ የታሪፍ ምጣኔ አፍሪቃውያን ነጋዴዎች በአህጉሪቱ ውስጥ የሚያከናውኑትን የወጪ ንግድ አዳጋች አድርጎባቸዋል ። የአፍሪቃ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና በሂደት የአገራቱን የውስጥ ንግድ ላይ የጣሉትን ታሪፍ ያስወግዳል። ይህም የአፍሪቃ ነጋዴዎች በአህጉሩ ውስጥ የሚያከናውኑትን ንግድ በተለይም የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት እንቅስቃሴ ለማሳለጥ ያስችላል ። ይሁን እና ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ተግዳሮቶችም አሉባቸው ። በጥናቶች የተለዩት በአፍሪቃም ሆነ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ አራት መሰረታዊ ችግሮች ናቸው። እነርሱም የገንዘብ አቅርቦት እጥረት፣ የመስሪያ ስፍራ ችግር፣ የገበያ ተደራሽነት ችግር እና የሙያ ክህሎት ብቃት ማነስ በዋናነት ይጠቀሳሉ። 

እነዚህን ችግሮች በመፍታት ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ከቀጠናው ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ከወዲሁ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አቶ ጌታቸው ተናግረዋል። ተቋማቱ ምን አይነት ምርት እና አገልግሎት ማን እንደሚፈልግ በግልፅ ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። ወቅቱን ያገናዘበ ተፈላጊ ምርት እና አገልግሎት ለማቅረብ የተዘጋጁ ሊሆን ይገባል። መንግስትም በሀገሪቱ ለሚንቀሳቀሱ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት አቅም በማጎልበት ፣ ተቋማትን በማጠናከር ፣ እና የብድር አቅርቦት ማጠናከር ይጠበቅበታል ።