Thursday 6 September 2018


የዜና ትንታኔ ዝግጅት መመሪያ



መግቢያ

ለዜና አዲስ ህይወት የሚሰጥ ትንታኔ ነው፡፡ የዜን ትንታኔ ለመስራት በደንብ መዘጋጀት ይጠይቃል፡፡ በመጀመሪያ ራስን በሚነሳው ጉዳይ ላይ ልዩና ጠቃሚ የመረጃ ምንጭ አድርጎ ማሰብ ይጠይቃል፡፡ በዚህ ዝግጅት ውስጥ የሚሰራውን ትንታኔ ስራ ሳቢ ከማድረግ ባሻገር ለቀጣይ ስራ የሚሆን የመጣጥፍ ሀሳብ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግልም ይችላል፡፡



በዜና ስራ ላይ ያለው ዋናው ትኩረት ዜናው ጊዜ አልፎበት ተገላጊነቱን እንዳያጣ መስራት ነው፡፡ በዜና ትንታኔ ቢሰራ ግን ግቡ የተዘገበው ዜና ለወደፊት ጭምር ጠቀሜታው እንዲዘልቅ ለማድረግ ነው፡፡ ለዚህም አንደኛው መንገድ ትኩረታችንን ወደፊት በሚሆነው ነገር ላይ ትንታኔያችንን ስንሰራ ነው፡፡ ሌላው በትንታኔያችን ውስጥ ያለፈውን ጊዜ አካተን መመልከት መቻልን ያካትታል፡፡

ስኬታማ የዜና ትንታኔ ስራ የሚከተሉትን ደረጃዎች የጠበቀ አሰራር ይከተላል፡፡

1.   ርዕስ መምረጥ - በመረጥነው ርዕስ/ትኩረት ዙሪያ ዜናዎችን በመለየት ማድመጥና መከታከል ከዚያም የተለያዩ ምንጮችን ማገላበጥ ሁልጊዜ አዲስ ነገር እንድናውቅ ይረዳናል፡፡ ለትንታኔ ስራችንም ትልቅ ግብአት ይሆነናል፡፡

2.   ታሪኩን መወጠን - የዘገባውን መቼት መለየት የመጀመሪያ ተግባር ይሆናል፡፡ ይህንን ክፍል በአጭሩ በማስቀመጥ የቀረውን ክፍል ለዋናው ጉዳይ በተለይ መያዝ ያስፈልጋል፡፡

3.   ትንተና መስጠት - በትንታኔያችን የምንሰራው ከላይ የመረጥነው የትኩረት ጉዳይ ከተለያየ እይታ የሚሰጠውን እንድምታና ምስል ለአድማጭ በመረጃ በማጣቀስ የማሳየት ስራ ነው፡፡ በዚህም ገለፃ በተነሳው ጉዳይ ላይ ብዙዎች የያዙትን ግንዛቤና እምነት እንዲቀይሩ ወይም አጠናክረው እንዲገፉበት ማስቻል አላማው ነው፡፡

4.   ትንበያን ማስቀመጥ - በጉዳዩ ላይ የወደፊት ክስተቶች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉና ያላቸውን የተፅዕኖ ደረጃ ለማሳየት መሞከርን በዚህ ተግባር ትኩረት ልንሰጠው የገባል፡፡ ይህ ተግባር በመጠኑ የሰፋ ሙያዊ ግንዛቤ መያዝን ስለሚጠይቅ በሀላፊነት ስሜት ሊሰራ ይገባል፡፡ ይህም ክፍተት ተገቢውን መረጃዎች ከተለያዩ ምንጮች በመሰብሰብ ማደራጅንና ማዋሀድን ይጠይቃል፡፡

5.   ትንተናውን መጠቅለል - መነሻ የነበረውን የትኩረት ዘገባ እንደገና በማስታወስ ከሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር ያለውን መስተጋብር ማሳየት በዚህ ደረጃ የሚተገበር ስራ ነው፡፡

ውጤታማ የዜና ትንታኔ ለመውጣት ስራውን የምንገመግምባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ሀ. ጠቀሜታ - ለትንነታኔ የተመረጠው ርዕሰ ጉዳይ ከአድማጭ አንፃር ጠቃሚ መሆኑን መለየት

ለ. የማይሞት - የማይሞት ይዘትን በማንሳት ለወደፊት አንባብያንና አድማጮች ፍላጎትን የሚያርፍበት እንዲሆን ማስቻል፡፡

ሐ. ከአድልዎ የፀዳ - ትንታኔው ወደ አንድ ወገን ያደላ መሆኑ ጎልቶ ተአማኒነትን እንዳያወርድ መጠንቀቅ፣ ጨለምተኝነትን ማስወገድ፣ የሞቱ ጉዳዮችን ማንሳትና ትፅዕኖኗቸው ከባድ የሆኑ ጉዳዮችን ሀላፊነት በጎደለው መልኩ መነካካት አግባብ አይደለም፡፡

መ. እውነት - መረጃ ይኑረን፡፡ በጊዜው ያሉ ጉዳዮች የአድማጮችን ትኩተር ይስባሉ፡፡ በመሆኑም እውነተኛ ነገርን በማንሳት ከአሉባልታ መራቅ ያሻል፡፡

ሠ. አሳዋቂ - ስድስቱን የ ‘ምን’ ጥያቄዎች በመመለስ ትንታኔው ሚዛኑን የጠበቀና የወደፊቱን አመላካች እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል ፡፡ (ምን፣ ማን፣ መቼ፣ የት፣ ለምንና እንዴት)

ረ. ብቸኛ ዘገባ - ለአድማጮች ሙሉ በሙሉ ልዩ ይዘት በማቅረብ ብቸኛ የዘገባው ምንጭ ለመሆን ማሰብና መስራት የስፈልጋል፡፡

ሰ. ዋጋ ያለው - የትንታኔ ዘገባው ባንጠለጠለው ትርፍ ጉዳይ ሳይሆን በጥልቀት ባነሳው ዘገባ ዋጋ እንዳለው መረጋገጥና ማሳየት፡፡
እነዚህን መገምገሚያ መስፈርቶች በመጠቀም የዜና ትንታኔያችንን ልዩ፣ አስተማሪና ጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን፡፡ ትንታኔ በተደጋጋሚ በመስራት ልምድን በማዳበር ጉዳዮችን በጥልቀት ለማየት ከማስቻሉም ባሻገር በጥሩ ተነሳሽነትና የአእምሮ ዝግጅት ላይ ለመድረስ ያስችላል፡፡  
A Training on Security Report Writing was underway for S&S Property Administration and Security Service

Content

What is a report?

How security report is different?

What a report entails?

Characteristics of good report

Types of security reports

Writing a regular/Duty report

Writing an incident report

Writing a maintenance report

Important issues of security report

Writing a report

Completing a report

Tips to improve security report

Retaining records of reports  

Tuesday 5 June 2018

የጋዜጠኛና ጋዜጠኝነት ተግዳሮቶች በአሁኑ ዘመን


የጋዜጠኛና ጋዜጠኝነት ተግዳሮቶች በአሁኑ ዘመን
ጌታቸው መላኩ
ግንቦት 23 2010
አዲስ አበባ

በዘመናችን ሰዎች ለቁጥር በሚያዳግቱ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ አነዚህም ለሰዎች የቀን ተቀን ኑሮ ገቢ ከሚያስገኙት እስካ ሙያዊና ህይወታዊ ጥሪ ሆነው የሚከወኑትን ስራዎች ያካትታል፡፡ ነገር ግን  በሁሉም ዘርፍ ውጤታማነት ተዋናዩን ሁሉ የሚያስደስት ነው፡፡

አንዳንድ ስራዎችን ጊዜና ሁኔታዎች ይገድቧቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ አላማቸውን በብቃት ሲያሳኩ አይታዩም፡፡ ለምሳሌ የማምረቻ ፋብሪካዎች የስራ ሰዓት አዋጅ፣ የሀይል አቅርቦት የድርጅቶቹ የስራ ሰዓት ስምሪት አቅምና ሌሎችም ነገሮች የገድቧቸዋል፡፡ ለእነዚህ ገዳቢ ኩነቶች ምላሽ በመስጠት የ24 ሰዓት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ጠቋማት እንዳሉ ያጤኗል፡፡
የሁሉም ተቋመት ግብ ቢያንስ በአላማ ደረጃ ግን አቅማቸውን አሟጣ በመጠቀም ውጤታማና ትርፋማ መሆን እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡
ተቋማት የሰዎች አስተሳሰብ መገለጫና ውጤት ናቸው፡፡ ከላይ የገለፅናቸው በተላያዩ ሁኔታዎች የተገደቡም ይሁኑ ለእነዚህ ሁኔታዎች ምላሽ ሰጥተው ሙሉ አቅማቸውን ለመጠቀም የሚታትሩ ተቋማት የመሪዎቻቸውና የሰራተኞቻቸው የአስተሳሰብ አይነትና ደረጃ መገለጫዎች ናቸው፡፡ በማናቸውም ሁኔታ ግን ስራን በውጤት መተርጎም በአስተሳሰብ ደረጃ የማንኛውም ተቋም ባልደረባ አላማና ፍለጎት ቢሆንም፤ ተግባራዊ መገለጫው ግን ግንዛቤ ደረጃውና በልምዱ ከሰዎች ሰዎች ይለያያል  አንዳንዴም ጭራሽ አይገጥምም፡፡
ባለንበት ዘመን ሰዎች ወደስራቸው ሲገቡ ባለፈው የስራ ቀን የጀመሩትን ዛሬ ለመቀጠልና የስራ ሰዓት እስኪገባደድ ጠብቀው ለመተግባር ከሆነ ችግሩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስለኛል፡፡ ማንኛውም ስራ የሚፈልገው የእውቀት የክህሎትና የአመለካካት ደራጃ የሚለያይ የማቀድና ውጤትን የማለም ተዘክሮ አለው፡፡ የውጤት ተኮር ስራ አመራር "በአጋጣሚ" ከቀየራቸው የጥበቃ ሰራተኞች ልምድ እንደተረዳሁት እምነታቸው የሚጠብቁት ንብረት በተሰማሩበት ቀንና ሰዓት አለመጉደሉን ማረጋገጥ ዋና ተግባራቸው ቢሆንም ንብረቱ ለስርቆት ሊዳረግ የሚችልበትን መንገድና አጋጣሚ ቀድሞ በመለየት አደጋን ቀድሞ ማስወገዱ ከተራ ሰራተኝነት የዘለለ ባለሙያ እንደሚያደርጋቸው አምነው ተቀይረዋል፡፡ በመሆኑም ስራ ከተራ የዕለት ከዕለት ተግባር ባለፈ ሙያዊ ተሰጥቶና አስተዋይነት ወደሚለካበት የአተገባበር ደረጃ  ካላደገ አሰልቺ፣ ውጤት አልባና በስተመጨረሻም ተጠያቂነትና ጉዳት ላይ የሚጥል ውጤት እንደሚመጣ እሙን ነው፡፡
እንዳንድ ስራ ዘርፎች ከሌሎች በተለየ እቅድ ሲሹ አንዳንዶች ደግሞ ልዩና ተገማች ባለሆኑ አጋጣሚዎችና ሁነቶች የተከበቡ በመሆኑ ለተግባራዊነታቸውና ውጤታቸው የተለየ ትኩረት ይሻሉ፡፡ ይህም የሚረጋገጠው በእቅድ ጊዜ በሚደረጉ ጥልቅ ግምገማዎች ነው፡፡
በታሪክና ባህል ከአለም ዋነኛዋ ሀገር የነበረችው ሀገራችን በዕድገትና በስልጣኔ ግን እስካሁን በዝግመት ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህም ዘመን የሶስተኛ ዓለም ሀገር ተብለን የምነጠራ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ (1990ዎቹ እ.አ.አ) አዳጊ ሀገር የሚል የማፅናኛ አይነት ስም ተለጥፎልናል፡፡
ይህ የሆነበት ምክንያት ለግምት የሚያዳግት ቢሆንም፤ ብዙዎች መረጃ እያጣቀሱና እየተነተኑ የየራቸውን ሀሳብ ያቀረቡበት ጉዳይ ስለሆነ ወደዚ መግባቱ ለጊዜው አስፈላጊ አይደለም፡፡ አንዱና ዋነኛው ችግር ግን ባለሙያነት የመጥፋቱና ስሜቱም  የመድከሙ ጉዳይ ሲሆን በዚህ ፅሁፍ ለማየት የተመረጠውም ይኸው ጉዳይ ነው፡፡ በዘመናችን ካለመው የጋዜጠኝነት ስራ ክዋኔ አንፃር እንደሚከተለው ታይቷል፡፡
ባለሙያ ማለት በቀላሉ ሙያን ገንዘቡ ያደረገ ማለት ነው፡፡ ሙያን ነጥለን ወስደን ስናይ ደግሞ ተግባርን በመለየት በመተንተን አቅዶ በተለያዩ መለኪዎች ውጤታማ የመሆን ስራን ያመለክታል፡፡ የስራ ዘርፍ ተመራማሪዎች የሙያተኛን ውጤታማነት በሶስት መለኪያዎች ይለኩታል፡፡ እነዚህም ጥራት፣ ብዛትና ጊዜ ናቸው፡፡ በመሆኑም የዘመናችን የጋዜጠኝነት ተግባር እንደ ስራ ሲታይ ጋዜጠኛው እንደባለሙያ ሲለካ ምን ይመስላል? በተለይተግዳሮቱስ ምንድን ነው?
በዘመናችን ያለ ጋዜጠኝነት ተግዳሮቶች መገለጫ ከሆኑት ተግባራት መካከል በዕለት ደራሽ ስራ መጠመድ፣ መረጃ ማግኘትን የስራው መጀመሪያና መጨረሻ አድርጎ መውሰድ፣ በጊዜ ሂደትና በጠንካራ ስነምግባር በሙያው የሚያድግ ባለሙያ እንደሚኖር መዘንጋትና ከግል አቅምና አቋም የዘለለ እይታ መገደብ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ከዚህ በመቀጠል እነዚህ አስተሳሰቦች እንዴት በሀገራችን የጋዜጠኝነት መህዳር ውስጥ ተግባራዊነታቸው እየሰፋ እንደመጣና ውጤታማነትን እየፈተኑ እንደሆነ እንመልከት፡፡
በእለት ደራሽ ስራ መጠመድ
ጋዜጠኛው የመስሪያ ቤት አደረጃጀት ሰለባ የሆነበት የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሀን ዘርፍ ዜናም ይሁን ዝግጅት በስምሪት የተባለ በሚመስል ተግባር እንደተጠመዱ ያመላክታል፡፡ በመሆኑም እቅድ ለይስሙላና ለስብሰበ ማጣፈጫ ከመወራቱ የዘለለ በመገናኛ ብዙሃን ተግባር የሰማይ ያህል የራቀ እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡
አሳሳቢው ጉዳይ ይህ ባህል ሆኖ በጀማሪ ባለሞያዎች ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተፅዕኖ ነው፡፡ ባለሞያዎች የጋዜጠኝነት ሞያ የዕለት ደራሽ ስራ የወጠረው ተግባር ሆኖ የዕቅድና የክትትል ዜናና ዘገባዎች ከጋዜጠኝነት ድርሳን እንዳይፋቁ የሚሰጋበት ዘመን ላይ እንደሆንን ብዙዎች ይነሳሉ፡፡
በድንገት ደራሽ ስራ መጠመድ የስራ መጀመሪያና መጨረሻ የሆነላቸው ጋዜጠኞች የዚህን ትግበራ ትሩፋቶች ከገፀ በረከትና ንዋይ ጥቅም አንስቶ ብዙ አውሪ ትንሽ ስሪ እንዳደረጋቸው ለማወቅ ከላይ የተጠቀሱትን መለኪያዎች በጥቂት ሞያተኞች ላይ በመተግበር ማየት ይቻላል፡፡
የስራን ክብደትና ቅለት የመለኪየው የሚያመጣው ውጤትና የሚፈጥረው ተፅዕኖ መሆኑ ቀርቶ ጋዜጠኛው ለጉዳዩ ጥንቅር የወሰደበት ጊዜና የጉልበት (በእንቅስቃሴና በማሰብ) መሆን መጀመሩ ከቀን ተቀን እንቅስቃያችን ማየት ጀምረናል፡፡
የእለት ደራሽ ስራ የፈጠራቸው ዕለት ደራሽ ጋዜጠኞች ተስፋና እርግማን በራሳቸውና በአስተማሪ አለቆቻቸው እጅ ነው፡፡ ቀደሞ የነቃና ተስፋውን የመረጠ ባለሙያ ቢኖር መጀመሪያ ማድረግ ያለበት ከዚህ አሰራር የሚወጣበትን ዕቅድ ለራሱና ለባልደረባው መስራት ነው፡፡
መረጃ ማግኘትን የሰራው መጀመሪያና መጨረሻ አድርጎ መውሰድ
በዘመናችን የማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን ይህንን ጉዳይ ፉርሽ ያደረጉት ቢመስልም ጋዜጠኛው አሁንም የዚህ ተግባር / አስተሳሰብ ተጎጂ ነው፡፡ብዙዎች ራሳቸውን ለመከላከል የማህበራዊ መገናኛ ብዙኃንን ተአማኒነትን እያብጠለጠሉ  መረጃቸው ያልተጣራና ሙያዊ ስነምግባር የጎደለው ነው እያሉ ቢያነሱም፤ ከእነሱ የበለጡ ብዙዎች ደግሞ ጭራሽ እነዚህኑ የመረጃቸው ምንጭ ሲያደርጓቸው ይስተዋላሉ፡፡
የዘመናችን ጋዜጠኝነት ሰበር ዜና ማቅረብ የቀደመ ምን ብላ ….. አይነት ጨዋታ አድርጎታል ፡፡ የዚህ ጨዋታ ተጎጂ ደግሞ ጋዜጠኛው ራሱ ነው፡፡
በእውነት መረጃ ማግኘት ብቻ የጋዜጠኝነት ስራ መጀመሪያውና መጨረሻው ይሆን?  አንድ የእንግሊዝናኛ አባባል አዘውትሬ በትምህርትና ስራ ላይ እጠቀማለሁ “የተፃፈ ሁሉ ሊጠየቅ እንጂ እንዲሁ ሊቀበሉት አይገባም” መረጃ ያገኘ ጋዜጠኛ ሁሉ ባለሙያ የሆነ እየመሰለው ለሞያውና ለራሱ ሃፍረት እየሸመተ ያለባቸው ተግባራት ከግዜ ወደ ግዜ እየተበራከቱ መጥተዋል ፡፡
ድህረ ገፅ ላይ ዜና ወይም ሃተታ ለጥፎ መልሶ ማንሳት፤ ያልተሟላ መረጃ አትሞ ማስተባበያ ለማውጣት መራወጥ፤ የማይወክል ጉዳይ አስተላልፎ የይቅርታ መግለጫ ለማንጋጋት መጣር የዘመናችን ጋዜጠኞች መገለጫ ከሆኑ ውለው አድረዋል፡፡
አንድ ጋዜጠኛ መረጃ ማግኘቱ መጀመሪያው ቢሆንም መረጃው ለታዳሚ የሚኖረውን ፋይዳ መመርመር ከቻለ ዕሴት ጨመረበት ፤ ከዚያም አልፎ አቀራረቡን አወቀበት ፡፡ ይህም ባለሞያ የሚያሰኘው ተግባር ይሆናል ፡፡ በቅርቡ በአንድ መገናኛ ብዙኃን የአንድ አካባቢ የአየር ሁኔታ ዘገባ ሲሰራ የቦታው ከፍተኛ የሙቀት መጠን 80 ዲግሪ ሴልሽየስ ነው ብሎ ያቀረበ ጋዜጠኛ አስታውሳለው፡፡
ይህ መሰረታዊ እውቀትን የሚፈትን ዘገባ የጋዜጠኛው የ"መረጃ መጀመሪያና መጨረሻ" ጉዳዩ የሰረፀበትን ደረጃ አመላካች ሲሆን አንድምታው ግልፅ ነው፡፡ መረጃ ለማግኘት መፈልፈል መበርበር የጋዜጠኛ ስራ ነው ፡፡ መመርመር መተንተንና ማበጠር ይከተላል ፡፡ በመጨረሻ ለታዳሚ እንደሚጠቅም ማቅረብ ይሰልሳል፡፡
ይህ የመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ተግባር ሀሁ መሆን ሲገባው በዕቅድ እንኳ ሊሰራ ያልቻለ ከፍተኛ ደረጃ ተግዳሮት ሆኖ በኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ድባብ ላይ ይታያል፡፡
በጊዜ ሂደትና ጠንካራ ስነምግባር በሙያው ያለማደግ
የመገናኛ ብዙኃን ከሌሎች የሙያ ዘርፎች የተቀዱ የስራ መደቦችና እርከኖች ሲጠቀሙ ይስተዋላል፡፡ ከጀማሪ ዘጋቢ እስከ ዋና አዘጋጅ ያሉ ስያሜዎችም የብዙዎች የደብዳቤ ሲያልፍም የመታወቂያ ወረቀት መገለጫዎች ሆነዋል፡፡ ይህ በራሱ ችግር ባይኖረውም በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ግን ሁሉም ተቀላቅሎ አንድ ሆኗል ፡፡ ይህንንም ያመጣው  “ጋዜጠኛ” የሚለው የውል ስም ይመስለኛል፡፡
የጋዜጠኝነትና የተግባቦት ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ከአጫጭር ስልጠናዎች ደረጃ ተነስቶ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ የሚሰራበት የትምህርት ዘርፍ ሆኗል የቀደሙት የመገናኛ ብዙኃን ማሰልጠኛ ተቋማትና ማሳያዎች ናቸው፡፡ዋናው ጉዳይ እነዚህ ተቋማት ባለሞያ ፈጥረዋልን? የሚለው ነው፡፡ ከሌሎች ሞያዎች ጋር ማነፃፀር የዚህ ፅሁፍ አላማ ስላልሆነ ወደዛ አልገባም፡፡
ነገር ግን ጋዜጠኝነት በግዜ ሂደትና በጠንካራ ስነምግባር በሙያ ልህቀት የሚታይበት ዘርፍ መሆኑ አጠራጣሪ እንደሆነባቸው ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ሙያ ከሚከፈል ተራ የስምሪት ይበልጣል ፡፡ ሞያ ወጣኒነት(ጀማሪነት) አዳጊነትና ብቁነት የሚታይበት የስብዕናና የአመለካከት መገለጫ ነው፡፡
ሙያ በዕቅድ ተሰርቶ የሚለወጡበትና የሚበቁበት ልዩ ፀጋ ነው፡፡ ሙያ መጨረሻ ለሌለው የእውቀት አለም ዜግነት ማግኛ መለያ ነው፡፡ በአገራችን ጋዜጠኝነት በአንድ ጀንበር ተንታኝ የሚኮንበት በሚቀጥለው ቀን መፍትሔ አመላካች ሊቅ የሚኮነንበት በሶስተኛ ቀን ያላየነው የለም የሚባልበት አሳዛኝ ዘርፍ ሆኗል ብለው ብዙዎች ያማርራሉ፡፡
ጋዜጠኝነት በታቀደና በተመረመረ ስራ የሚያድጉበትና በስብዕና የሚበለፅጉበት አልፈውም ለታዳሚ እሴት የሚሆኑበት ምዕራፍ ሊዘጋ አንድ እሁድ ቀረው ብለው ያዝናሉ ይቆጫሉ፡፡ በመሆኑም ጋዜጠኝነት በግዜ ሂደትና በጠንካራ ሞያዊ ስነምግባር ለማደግ የማይተጋበት ዘርፍ ለምን ሆነ ብለው ቢጠይቁ መልሱ ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም ይመስለኛል፡፡
በዕቅድ መመራትና በውጤት መለካት ከጋዜጠኝነት መንደር ኮብልለዋል፡፡ ይኽውም ለአቋራጭ መንገድ ተጠቃሚዎች በሩን በሰፊው ከፍቷል፡፡ ብዙዎች የባለስልጣናት ረዣዥም እጆችና የፖለቲካ ስርዓት ተፅዕኖዎችን በመጥቀስ ችግሩን በሌሎች ሊያላኩ ቢሞክሩም በራሳቸው መከራከሪያ ነጥብ ራሳቸውን ይጠልፋሉ፡፡ ባለቤቱ ያቀለለውን እንዳልን ከላይ!!
ከግል አቅምና አቋም ያልዘለለ ዕይታ
ዘመኑ ለጋዜጠኞች ዶሮ ብታልም ጥሬዋን ነው የሆነባቸው ይመስለኛል፡፡ ዕውቀትን በራሳቸው ትንሽ ቁና የሚሰፍሩ፣ መረጃን በራሳቸው የዕይታ አድማስ ውስጥ የሚፈልጉና፣ ጥበብን በራሳቸው የዕውቀት አድማስ ልክ ብቻ የሚተነትኑ ጋዜጠኞች በዝተዋል ብቻ አይገልፀውም፡፡ በእርግጥ አንድ እውነታ አለ አንድ ስራ መጀመሪያ ሰሪውን ካላረካ ሌላውን ያረካል ለማለት ይከብዳል፡፡
ነገር ግን ሰሪውና ስራው ማንና ምን ናቸው? የሚለውን እዚህ ጋር ማጤን ያስፈልጋል፡፡ በአንድ አጋጣሚ አንድ ጋዜጠኛ ጣቢያው የሰራው ልዩ ፕሮግራም ከሌላው የተሻለ እንደሆነ ሲገልፅልኝ የተየኩት አንድ ጥያቄ ብቻ ነበር እርሱም “በማን መለኪያ” የሚል ነበር በሰሩት ስራ መርካት ችግር የለበትም ችግሩ የሚጀምረው የሰሩት ስራ ለሌሎች ስራዎች ማንፀሪያነት የደረሰ የመጨረሻ ተግባር ነው ብለው የወሰዱት ግዜ ነው፡፡ በመሆኑም ጋዜጠኞችና መገናኛ ብዙኃን በራሳቸው አቅም ልክ ታዳሚን መገመት ሲጀምሩ የመጨረሻው መጀመሪያ ይሆናል፡፡
የዘመናችን ጋዜጠኞች ሌላው ችግር የግል አቋምን የአብዛኛው አቋም አድርጎ መሳል ነው፡፡ ይህ ነገር ካለማስተዋል ከሆነ በምክርና በትችት ሊስተካከል ይችላል ነገር ግን ሆን ተብሎ የተሰራ ከሆነ መመለሻው አደገኛ ማጣፊያው አጭር ይሆናል፡፡ የዚህ ፅሁፍ አንባቢም ይህ ትንተና በአቅምና በአቋም ላይ ተመስርቶ በበጎ ለበጎ የተዘጋጀ እንደሆነ ይረዳው ዘንድ እለምናለው፡፡
የጋዜጠኞች ከግል አቅምና አቋም ያልዘለለ ዕይታ የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ከላይ እንደተገለፀው አንዱና ዋነኛው መረጃ ማግኘትን የመጀመሪያና የመጨረሻው አድርጎ መውሰድ ነው፡፡ በመሆኑም መረጃን ለመጠየቅና ልምድ ያለመኖር የአቅም ውስንነትን ያመጣል፡፡
ሌላው ምክንያት በግዜ ሂደትና በጠንካራ ስነምግባር በሙያው ያለማደግ ነው፡፡ በመሆኑም ጋዜጠኞች ጉዳዮችና የመመርመርና የመተንተን ችሎታና ፍላጎት ሲከዳቸው አቋም አራማጆች ሆነው ያርፉታል፡፡  ዘወትር እንደሚነሳው ሁነኛ የቃለመጠይቅ ጥያቄ ማዘጋጀት እየተሳናቸው ጥያቄዎቻቸው "ምን ይላሉ?" እና "ምን ይሰማዎታል?" የሚል ይሆናል፡፡
አንዱ ጋዜጠኛ አንድ እንግዳውን ምን ይሰማዎታል ብሎ ቢጠይቅ ችብግዳው "ንዴት" ብሎ መለሰለት መልሱ ያልተዛመደለት ጋዜጠኛ "በምን?" ቢለው "በአንተ ተራ ጥያቄ" ብሎት ሄደ የሚል ቀልድ ብዙዎቻችን የሰማን ይመስለኛል፡፡
ምን ይሻላል?
ጋዜጠኝነት በእለት ደራሽ ስራ ብቻ የመጠመድ አባዜ አይደለም፡፡ ነገር ግን ጋዜጠኝነት በጊዜ ሂደትና በጠንካራ ስነ ምግባር በሙያ የሚያድጉበት፣ መረጃ ማግኘት የስራው መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ ያልሆነበት፤ ይልቁንም ከግል አቅምና አቋም የዘለለ ሰፊ ሞያዊ ዕይታን የሚፈልግ መመርመርን የሚሻና አዘውትሮ መጠየቅን የሚያስገድድ ተግባር ነው፡፡
በመሆኑም ይህ ጉዳይ የማይሆንበት ሁሉ አቋርጦ ቢመለስ፤ ለመቆየት የወሰነ ካለ ግን የስራውን ባህርይ ተገንዝቦ ራሱን ማትጋት ይገባዋል፡፡ የስራ መሪዎች ፤ የትምህርትና የስልጠና ተቋማት በዘርፉ የቆዩ ባለመያዎች ራሳቸውን የሚፈትኑበት ጊዜ ቢያልፍም "ከመቅረት መዘግየት ይሻላል" እንዲሉ በቀረው ጊዜ ሁኔታዎችን ለማስተካከል ቢሰራ መልካም ነው፡፡
ምን ይሰራ?          
"እዳው ገብስ ነው" ይባላል ችግሩ በሌሎቹ ዘርፎችም እንዳለ ሁሉ የሙያውን አላማ ጠንቅቆ ማወቅ የብዙሃን መገናኛዎች ራዕይና አላማ አበጥሮ መለየትና ከሚሰሩት ስራ ሁሉ ውጤቶችን መጠበቅ ናቸው፡፡ አንደኛ ራስን መለወጥ ሁለተኛ ሌላውን /ታዳሚን ለመለወጥ ማቀድ፡፡
ይህስ ከሆነ በኋላ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ማለት ነው? ውጤታማነት ይጎላል ማለት ነው? መልሱ "ይሆን ይሆናል" ይመስለኛል ፡፡ በእርግጠኝነት የሚታወቀው ደርሰን ስናየው ብቻ ነው፡፡ ሌሎች ሄደዋላ!!

Thursday 17 May 2018

ዶ/ር አብይ አህመድ ፓርላማ ንግግር አንድምታ
ጌታቸው መላኩ
ዶ/ር አብይ አህመድ በፓርቲያቸው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዬታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ተመርጠው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ ቃለ መሀላ በመፈፀም የርዕሰ መስተዳደሩን ቢሮ ከአቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም መረከባቸው ይታወሳል፡፡
ዶ/ር አብይ በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሀላቸውን በመፈፀም በይፋ ስራቸውን ሲጀምሩ ባደረጉት ንግግር በደምሳሳው በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ያለን ጉዳይ ነክተዋል በማለት ብዙዎች ሲያመሰግኗቸው ለማስተዋል የግዴታ የማህበራዊ ብዙሀን መገናኛ መንገዶች አባል ወይም ተጠቃሚ መሆን አይሻም፡፡ ግለሰቡ ኢትዮጵያዊነት ከሚለው ትልቁ ጉዳይ አንስተው በየስራ ዘርፋችን ባለፉት ጊዜያት ያሳለፍነውን የባከነ ጊዜ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመስራት እንድንተጋ አሳብበውናል፡፡ ይኸውም በዋናነት በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በተከሰቱ ተቃውሞዎች የባከኑ ጊዜያትን ያመላከተ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ነገር ግን በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አጐራባች ነዋሪዎች እንዲሁም በሌሎች መለስተኛ ችግሮች የተነሱባቸውን የደቡብና የጋምቤላ ክሎችንም የሚያካትት እንደሆነ ግን ለማጤን ጉዳዩን ለተከታተለ ሰው በግልፅ የሚታየው ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ጠ/ሚው የተጎዱ ወገኖችን ለማሰብ በዚህ ንግግራቸው ቢኖርም መዘግየታቸው ምን አለ እንድንል ያሳስበናል፡፡
የንግግራቸው ልዩነት ለእኔ በተለየ ባይሰማኝም ብዙ አድማጮች ከሌሎች ቀዳሚ መሪዎች (በተለይ በኢህአዴግ) ዘመን ተዘውትረው አልተሰሙም ያሏቸውን ገለፃዎችና ቃላት ስለሰሙ እንደሆነ ብዙዎችን አነጋገሬ የተገነዘብኩት ጉዳይ ነው፡፡ ይህን በይበልጥ ለማየት የንግግራቸውን የመገመሪያ ሶስት ደቂቃ ይዘት በመዳሰስ የሚቀጥለውን ንባብ ለማቅረብ ገፋፍቶኛል፡፡ ይህ የንግግር ትንታኔ አሰራር በሌላው አለም ከተራ ትንታኔነት አልፎ አመላካች ተግባርና በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ጭምር የሚሰጥበት ዘርፍ እንደሆn (though not like cryptology) ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ በሀገራችንም ቢለመድ የተሻለ ግንዛቤ ያመጣል፡፡
ዶ/ር አብይ የመጀመሪያ ነጥብ አድርገው ያነሱት የሥልጣን ሽግግሩ የመጀመሪያው ሰላማዊ ሽግግር እንደሆነ በማስመር ነው፡፡ ነገር ግን ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሣለኝ ስልጣናቸውን የለቀቁት የተፈጠረ ችግር ስላለ የመፍትሔ አካል ለመሆን አስበው እንደሆነ የገለፁትን ለማስተባበል የመጣ አነጋገር ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ጠ/ሚ ሀይለማርም ከስልጣን አልወርድም ቢሉ ምን ይፈጠር ነበር? እርሳቸውስ ስልጣን የለቀቁት ፈልገው ነው ወይስ ተገፍተው? ስልጣን ባይለቁ ምን ይከሰት ነበር? እውነትስ አንድ የፖለቲካ መሪ አይደለም ክፍል አለቃ የሚፈተነው አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በመጋፈጥና በቆራጥ አመራር በመሻገር አይደለምን? ታዲያ ጠ/ሚ ሀይለማርያም ምን ነክቶአቸው ነው አንደዚህ በድንገት ዘጭ ያሉት፡፡ እዚህ ላይ ግልፅ ጦርነት አለመኖር የሰላም መኖርን አያመላክትም የሚለውን አባባል ልብ ይላል፡፡ የዶ/ር አብይ ንግግር ዝግጅት በዚህ መልክ መጀመሩ ግን የተለመደ መንገድ ስለሆነ የተለየ ነው ለማለት ይከብደኛል፡፡
የዶ/ር አብይ ቀጣይ የንግግር ይዘት ይህንኑ ጉዳይ በማንሳት የጠ/ሚ ኃይለማርያም ስልጣን የመልቀቅ ጥያቄን ለግለሰቡ የመከበር ጅማሮ እንዲሆን በሚያሳስብ መልኩ አስቀምጠዋል፡፡ ጉዳዮች በጊዜ ሂደት የሚጠሩ ቢሆኑም የመፍትሄ አካል ለመሆን በኢህአዴግ ውስጥ የተለየ ሰው በመምረጥ እንዴት ይመጣል የሚለውን ለመስማት በደርግ ዘመን የተፈጠረውና ሁሉም የደርግ ባለሥልጣናት ኮ/ል መንግሥቱን ጨምሮ አናውቅም ያሉት የ60ዎቹ ሰዎች ግድያ በደብዳቤ ተደግፎ በቅርቡ ይፋ እንደሆነ እንዳየን ልብ ይሏል (የደብዳቤ ማስመሰል ሊኖር እንደማይችልም እጠራጠራለሁ)፡፡
በሦስተኛ ደረጃ ዶ/ር አብይ ያተኮሩት በሥልጣን ሽግግሩ የተጉትን ማመስገን ላይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ዶ/ር አብይ በግልፅ የጠቆሙት ግለሰብ ወይም ቡድን ባይኖርም የኢህአዴግ ምክር ቤትንና የእህት ድርጅቶችን በተለይም ለእሳቸው በፍጥነት ለዚህ መታጨት የተጉትን የሚመለከት ይመስላል፡፡ ዶ/ር አብይ ከኢህአዴግ ም/ሊቀ-መንበርነት ወደ ሊቀ-መንበርነት ሲመጡ ለማ መገርሳ ወደ ፌዴራል ስልጣን ለመምጣት በተግበራ የማይገድ በሂደት ግን አወዛጋቢ ሊሆን የሚችል ህጋዊ ሁኔታ ስላለ ቢመስልም ኢህአዴግ ለህግና ለስርዓት ባይሆን ከአሁን በኋል ግድ እነደሚኖረው ለማሳት እንደሚችል በመለየት ነው፡፡ እዚህ ላይ ታዲያ ተመዞ የሚወጣው ጉዳይ እውነተኛው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ወይስ አቶ ለማ? ነገር ግን አንድ ነን ካሉ አንድ ነን፡፡ እዚህ ላይ በዶ/ር አብይ ንግግር ላይ የቃላት መደነቃቀፍ እንዳለ ያጤነ ሰው ካለ ሌላም ግንዛቤ ሊወስድ ይችላል፡፡
በመቀጠል ዶ/ር አብይ የሥልጣን ሽግግሩን “አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ የመጀመሪያ ሌላ እድል” ሲሉ ገልፀውታል፡፡ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ከምን አንፃር? የሚለው የሁሉም ጥያቄ ቢሆንም ዶ/ር አብይ በደፈናው የመግባባትና የአንድነትን ስሜት የመገንባት ጉዳይ በሚል አልፈውታል፡፡ አድማጭ ግን የበለጠ ጠልቆ መጠየቅና መመርመር ይገባዋል፡፡
አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ከምን አንፃር ከርዕዬተ-አለም ለውጥ ወይስ ሌላ? ያልታሰበ ጉዳይ አለ፡፡ እዚህ ላይ ጠ/ሚ ኃይለማርያም የድርጅት አባል ያልሆኑ ባለሙያዎችን የመሳብ ሥራ እንደ ጀመሩ ዶ/ር አብይ ደግሞ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ወደካቢኔ ለመሳብ አስበው ይሆን እንዴ? የሚል መላምት ቢታሰብ አንደሀሳብ መልካም ይመስለኛል፡፡ ይህስ ቢሆን አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ሊያስብል የሚችል ነገር ይኖረው ይሆን?
ዶ/ር አብይ “አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ የመጀመሪያ ሌላ እድል” ሲሉ ከዚህ በፊት የነበሩት እድሎች የትኞች ይሆኑ? አንባቢ ማጤን ያለበት የተባለው አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ከሆነ ብያኔው ከስልጣን ሽግግር ባለፈ የተለየ መንገድን መከተል ወይም የተለየ አመለካከት ያለውን ተቃዋሚ/ተፎካካሪ የመቀበልና የማሳተፍን ጉዳይ ይመለከት ይሆን? ሌላ እድልስ የተባለው ከየትኞቹ ያለፈ እድሎች አንፃር ነው? 1997 ምርጫ፣ የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ህልፈት፣ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት፣ የደርግ መንግሥት ውድቀት? የትኛው? ለትርጉም የቸገረ አገላለፅ ነገር ግን የታሰበበት! በእኔ ግምገማ የዶ/ር አብይ ንግግር ዋናው ማጠንጠኛው ይህ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡
ለማጠቃለል ዶ/ር አብይን ያመጣቸው እድል ወይስ ትጋት? ትልቁ ጥያቄ ነው፡፡ እድል እንዳመጣቸው የሚያምኑ ከሆኑ እድላቸውን በመጠቀም ለራሳቸው የተሻለ የሚሉትን ለመስራት እንደሚተጉ ግልፅ ነው፡፡ ዋናው ነገር “የተሻለ” የተባለው ነገር ለሁም “የተሻለ” እንዲሆን መመኘት ነው፡፡

Wednesday 16 May 2018




The Tripartite High level meeting between Ethiopia, Sudan and Egypt has reached an agreement following the meeting yesterday. 

Our Egyptian brothers are taking one more steps. We appreciate this as it is a demonstration of productive and matured diplomacy!!!


The Tripartite High Level Ministerial Meeting of Ethiopia, the Sudan and Egypt concluded @ 3AM (after midnight). 
Agreements have been reached:
- To establish tripartite Infrastructure fund,
- To establish independent, National, Scientific Study group to study the filling of the GERD,
- To present queries & observation to the Consultancy. 


DEAR READER,

It has been quite a busy time last year an i was not able to post contents so far.

I AM BACK