የዜና ትንታኔ ዝግጅት መመሪያ
መግቢያ
ለዜና አዲስ
ህይወት የሚሰጥ ትንታኔ ነው፡፡ የዜን ትንታኔ ለመስራት በደንብ መዘጋጀት ይጠይቃል፡፡ በመጀመሪያ ራስን በሚነሳው ጉዳይ ላይ ልዩና
ጠቃሚ የመረጃ ምንጭ አድርጎ ማሰብ ይጠይቃል፡፡ በዚህ ዝግጅት ውስጥ የሚሰራውን ትንታኔ ስራ ሳቢ ከማድረግ ባሻገር ለቀጣይ ስራ
የሚሆን የመጣጥፍ ሀሳብ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግልም ይችላል፡፡
በዜና ስራ ላይ ያለው ዋናው ትኩረት ዜናው ጊዜ አልፎበት ተገላጊነቱን
እንዳያጣ መስራት ነው፡፡ በዜና ትንታኔ ቢሰራ ግን ግቡ የተዘገበው ዜና ለወደፊት ጭምር ጠቀሜታው እንዲዘልቅ ለማድረግ ነው፡፡ ለዚህም
አንደኛው መንገድ ትኩረታችንን ወደፊት በሚሆነው ነገር ላይ ትንታኔያችንን ስንሰራ ነው፡፡ ሌላው በትንታኔያችን ውስጥ ያለፈውን ጊዜ
አካተን መመልከት መቻልን ያካትታል፡፡
ስኬታማ
የዜና ትንታኔ ስራ የሚከተሉትን ደረጃዎች የጠበቀ አሰራር ይከተላል፡፡
1.
ርዕስ መምረጥ - በመረጥነው ርዕስ/ትኩረት ዙሪያ ዜናዎችን በመለየት ማድመጥና
መከታከል ከዚያም የተለያዩ ምንጮችን ማገላበጥ ሁልጊዜ አዲስ ነገር እንድናውቅ ይረዳናል፡፡ ለትንታኔ ስራችንም ትልቅ ግብአት ይሆነናል፡፡
2.
ታሪኩን መወጠን - የዘገባውን መቼት መለየት የመጀመሪያ ተግባር ይሆናል፡፡
ይህንን ክፍል በአጭሩ በማስቀመጥ የቀረውን ክፍል ለዋናው ጉዳይ በተለይ መያዝ ያስፈልጋል፡፡
3.
ትንተና መስጠት - በትንታኔያችን የምንሰራው ከላይ የመረጥነው የትኩረት ጉዳይ
ከተለያየ እይታ የሚሰጠውን እንድምታና ምስል ለአድማጭ በመረጃ በማጣቀስ የማሳየት ስራ ነው፡፡ በዚህም ገለፃ በተነሳው ጉዳይ ላይ
ብዙዎች የያዙትን ግንዛቤና እምነት እንዲቀይሩ ወይም አጠናክረው እንዲገፉበት ማስቻል አላማው ነው፡፡
4.
ትንበያን ማስቀመጥ - በጉዳዩ ላይ የወደፊት ክስተቶች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉና
ያላቸውን የተፅዕኖ ደረጃ ለማሳየት መሞከርን በዚህ ተግባር ትኩረት ልንሰጠው የገባል፡፡ ይህ ተግባር በመጠኑ የሰፋ ሙያዊ ግንዛቤ
መያዝን ስለሚጠይቅ በሀላፊነት ስሜት ሊሰራ ይገባል፡፡ ይህም ክፍተት ተገቢውን መረጃዎች ከተለያዩ ምንጮች በመሰብሰብ ማደራጅንና
ማዋሀድን ይጠይቃል፡፡
5.
ትንተናውን መጠቅለል - መነሻ የነበረውን
የትኩረት ዘገባ እንደገና በማስታወስ ከሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር ያለውን መስተጋብር ማሳየት በዚህ ደረጃ የሚተገበር ስራ ነው፡፡
ውጤታማ
የዜና ትንታኔ ለመውጣት ስራውን የምንገመግምባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ሀ.
ጠቀሜታ - ለትንነታኔ የተመረጠው
ርዕሰ ጉዳይ ከአድማጭ አንፃር ጠቃሚ መሆኑን መለየት
ለ.
የማይሞት - የማይሞት ይዘትን በማንሳት
ለወደፊት አንባብያንና አድማጮች ፍላጎትን የሚያርፍበት እንዲሆን ማስቻል፡፡
ሐ.
ከአድልዎ የፀዳ - ትንታኔው ወደ
አንድ ወገን ያደላ መሆኑ ጎልቶ ተአማኒነትን እንዳያወርድ መጠንቀቅ፣ ጨለምተኝነትን ማስወገድ፣ የሞቱ ጉዳዮችን ማንሳትና ትፅዕኖኗቸው
ከባድ የሆኑ ጉዳዮችን ሀላፊነት በጎደለው መልኩ መነካካት አግባብ አይደለም፡፡
መ.
እውነት - መረጃ ይኑረን፡፡ በጊዜው
ያሉ ጉዳዮች የአድማጮችን ትኩተር ይስባሉ፡፡ በመሆኑም እውነተኛ ነገርን በማንሳት ከአሉባልታ መራቅ ያሻል፡፡
ሠ.
አሳዋቂ - ስድስቱን የ ‘ምን’ ጥያቄዎች
በመመለስ ትንታኔው ሚዛኑን የጠበቀና የወደፊቱን አመላካች እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል ፡፡ (ምን፣ ማን፣ መቼ፣ የት፣ ለምንና እንዴት)
ረ.
ብቸኛ ዘገባ - ለአድማጮች ሙሉ በሙሉ
ልዩ ይዘት በማቅረብ ብቸኛ የዘገባው ምንጭ ለመሆን ማሰብና መስራት የስፈልጋል፡፡
ሰ.
ዋጋ ያለው - የትንታኔ ዘገባው ባንጠለጠለው
ትርፍ ጉዳይ ሳይሆን በጥልቀት ባነሳው ዘገባ ዋጋ እንዳለው መረጋገጥና ማሳየት፡፡
እነዚህን መገምገሚያ መስፈርቶች በመጠቀም የዜና
ትንታኔያችንን ልዩ፣ አስተማሪና ጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን፡፡ ትንታኔ በተደጋጋሚ በመስራት ልምድን በማዳበር ጉዳዮችን በጥልቀት
ለማየት ከማስቻሉም ባሻገር በጥሩ ተነሳሽነትና የአእምሮ ዝግጅት ላይ ለመድረስ ያስችላል፡፡
No comments:
Post a Comment